admin
Sun, 01/26/2025 - 23:24
ለማህበረሰቡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ የሚያበረክት በተለያዩ የሙያ መስኮች ብቁ ዜጋ ለማፍራት እየተደረገ ባለው ጥረት ኮሌጁ የአንበሳውን ድርሻ እየተወጣ ነው ተባለ
ጥቅምት 20/2017 ቅበት ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን
የቅበት ከተማ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ከስልጤ ዞን ቴክኒክ ትምህርት ስልጠና ክፍል በጋራ በመሆን 12ኛ ክፍል ውጤት ያልመጣላቸው ተማሪዎችን በከተማ አስተዳደሩ በሚገኘው ማሰልጠኛ ተቋም በተለያዩ የሙያ መስኮች ትምርህታቸውን በመከታተል ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ ያለመ በ Mindset እና ሞቢላይዜሽን ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል
ስልጠናውን የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ቢሮ የኢንተርፕሬነር ዘርፍ ሀላፊ አቶ ረሻድ ከድር ሰጥተዋል።
በስልጠናው ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የስልጤ ዞን ቴክኒክና ሙያ መምሪያ ኃላፊ አቶ ፈድሉ ከድር፤ ተማሪዎች ወቅቱ የሚጠይቀውን የሙያ ትምህርት ክህሎት በአቅራቢያቸው በሚገኘው ኮሌጅ ላይ በመማር ብቁና ተወዳዳሪ ሊሆኑ እንደሚገባ አመላክተዋል።
በኮሌጁ ዘመኑን የዋጀና ሰልጣኞችን የተለያዩ የሙያ መስክ ላይ ክህሎት የሚያገኙበት ስልጠና እየተሰጠ ነው ያሉት አቶ ፈድሉ፤ በከተማ አስተዳደሩ እንዲሁም አጎራባች ወረዳዎች ላይ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች በሚፈልጉት የሙያ መስክ በመሰልጠን ተፈላጊነታቸውን ሊያሰፉ ይገባልም ነው ያሉት።
የቅበት ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ከድር ሁሴን በበኩላቸው በከተማ አስተዳደሩና በአጎራባች ወረዳዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ባለማምጣት እንዲሁም በሌሎችም ምክንያቶች ከትምህርት ገበታ ውጪ በመሆናቸው ፤ በአቅራቢያው ባለው ኮሌጅ በመመዝገብ በመረጡት የስልጠና መስክ ላይ የሙያ ባለቤት ሊሆኑ እንደሚገባ አመላክተዋል።
ኮሌጁ በማህበረሰቡ ከፍተኛ ፍላጎት መቋቋሙን ያነሱት ዋና የመንግስት ተጠሪው፤ በአጠገባቸው ባለው ፀጋ ሰልጥነው ራሳቸውንና ቤተሰባችን የሚለውጡ ሰልጣኞ ሊፈሩ እንደሚገባም ተናግረዋል።
ኮሌጁ በተለያዩ የሙያ መስኮች ከሚሰጠው ያለቀ አገልግሎት አንጻር ያለው የሰልጣኝ ቁጥር አነስተኛ ነው ያሉት አቶ ከድር በጥቂት ቀናት ውስጥ በየአካባቢው ግንዛቤ ያገኙ ሰልጣኞች ለሌሎች በማስተማር የሰልጣኞችን ቁጥር በሚፈለገው መጠን ልናሳድግ ይገባልም ነው ያሉት።
አቶ ከድር አክለውም ከተማ አስተዳደሩ ከኮሌጁ ጋር በመሆን ሰልጣኞችን ለመደገፍ እንደሚሰራ ገልፀዋል።
የስልጠናው የተሳተፉት ተመሪዎች እንደገለፁት ስለጠናው የኮሌጅ የሙያ ትምህት ላይ የነበረባቸውን የግንዛቤ ውስንነት ለመቅረፍ እንደሚያግዛቸውና በቀጣይ ለሌሎችም ግንዛቤ በመፍጠር በኮሌጁ የሙያ ባለቤት ለመሆን እንደሚሰለጥኑ አብራርተዋል።
በስልጠናው የስልጤ ዞን ቴክኒክና ሙያ መምሪያ ኃላፊ አቶ ፈድሉ ከድር፣የቅበት ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ከድር ሁሴን፣ረዳት የመንግስት ተጠሪዎች አቶ አብዱልፈታህ ላሌና አቶ ሸይቾ ሙስጠፋ፣የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ቢሮ የኢንተርፕሬነር ዘርፍ ሀላፊ አቶ ረሻድ ከድር ፣ተማሪዎችና ሌሎችም ተሳትፈል።
Image

Title
ለማህበረሰቡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ የሚያበረክት በተለያዩ የሙያ መስኮች ብቁ ዜጋ ለማፍራት እየተደረገ ባለው ጥረት ኮሌጁ የአንበሳውን ድርሻ እየተወጣ ነው ተባለ