Skip to main content

                                                  Background of Kibet Construction and Industrial College

  •   የቅበት ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ የሚገኘው ከመዲናችን አዲስ አበባ በስተደቡብ 147.1 ኪሎ ሜትር ርቀት በሰአት 3 ሰአት ከ19 ደቂቃ የሚፈጅ ሲሆን ከዞኑ ዋና ከተማ ወራቤ ደግሞ በስተሰሜን 28 ኪሎ ሜትር ርቀት በቅበት ከተማ አስተዳደር የሚገኝ ሲሆን የተመሰረተው በኢትዮጵያ አቆጣጠር ግንቦት 2013 ዓ/ም /2021 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በቀድሞው ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች ክልል መንግስት በሆነው ቴ/ሙ/ት/ስ/ቢሮ እውቅና በማግኘት በውስጡ 15 አስተዳደርና 9 አሰልጣኞችን በድምሩ 24 የሰው ሀይል በሟማላት በሶስት የሙያ መስኮች 102 ሰልጣኞችን በመቀበል ስራ ጀምሯል፡፡ 
  •   ተቋሙ የሰው ሀይሉን በማስፋት 20 አሰልጣኝ እና 26 አስተዳደር ሰራተኛ በድምሩ 46 የሰው ሀይል በማሰደግ እንዲሁም ደግሞ የሙያ መስኮችን በመጨመር እና የስልጠና ፕሮግራሞችን በማስፋት በመደበኛ፣በማታ፣በቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በአጫጭር ግዜ ፕሮግራሞች ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል፡፡ በነዚህ ፕሮግራሞች 350-400 ሰልጣኞችን በመቀበል ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
  •   በቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን ዘርፍ የማህበረሰባችንን ችግር ሊቀርፍ የሚችል ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠርና ኢንተርፕራይዞችን በመደገፍ ተወዳደሪ እንዲሆኑና ወደ ተሸላ ምርታማነት እንዲመጡ ሰፊ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡
  •   በተጨማሪም ተቋሙን ለማዘመን ሰፊና ዘመኑን የወጃ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡ለአብነትም ተቋሙ የራሱን ዌብሳይት በማበልጸግ ተቋሙን ዲጂታላይዝ ማድረግ ፣በካይዘን ማዘመን፣ዲጂታል ላይብረሪ መመስረትና ኦንለይን ሬጅስትሬሽን/ምዝገባ ለማካሄድ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡